የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር መግለጫ10 ግንቦት 2001ሰኞ፣ ግንቦት 10 2001ባለፈዉ ሰሞን የአሜሪካ መንግስት የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያለዉ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ አሳሳቢ ነዉ በማለት ባወጣዉ ዘገባ የኢትዮጵያን መንግስት መዉቀሱ ይታወሳል።https://p.dw.com/p/HsuVምስል AP GraphicsBank/DWማስታወቂያየኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በተደጋጋሚ በዘገባዉ የተካተቱ ማስረጃዎች ተቀባይነት እንደሌላቸዉ ሲገልጽ ቆይቷል። ዛሬም በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን አማካኝነት በሰጠዉ መግለጫ ወቀሳዉ በአሉባልታ ላይ የተመሰረተና ከሃቅ የራቀ ሲል በድጋሚ አጣጥሏል። ታደሰ እንግዳዉ/ሸዋዬ ለገሠ/ሂሩት መለሰ