የኮሎኝ ታሪካዊ ቤተ-መዘክር ተደረመሰ
ዓርብ፣ የካቲት 27 2001ማስታወቂያ
ኮሎኝ ከተማ ውስጥ፥ ጥንታዊ መዛግብትን ያከማቸ ታሪካዊ ቤተ-መዘክር ማክሰኞ ለት በድንገት መደርመሱ ተዘግቧል። ህንፃው ከተደረመሰ ቀናት ቢያስቆጥርም፤ ፍራስራሹ ውስጥ እንደተቀበሩ የተገመቱት ሁለት ሰዎችን የማዳን ተግባር ግን እስካሁን አልተጀመረም። በተደረመሰው ሕንፃ አካባቢ የሚገኙ ሌሎች ሕንፃዎች እንዳይደረመሱም ተሰግቷል። ቀድሞ አራት መቶ ሚሊዮን ዩሮ ዋስትና የተገባለት ይህ ታሪካዊ ቤተ-መዘክር በውስጡ ያከማቻቸው ጥንታዊ መዛግብት እንዳይበላሹ ርብርብ እየተደረገ ነው።