የኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ ህልፈት
ማክሰኞ፣ መስከረም 10 2009ማስታወቂያ
የኔልሰን ማንዴላ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሥልጠና “እጅግ ምሥጢራዊ ነበር” ሲሉ መናገራቸዉን ኔልሰን ማንዴላ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ኮሎኔል ፈቃዱን ዋኬኔን በመጥቀስ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዉላቸዋል ። የዝያን ጊዜዉ የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ የ«ANC» የትጥቅ ትግል ክንፍ አዛዥ ሆነዉ ለስብሰባ ከዚያም ለስልጠና ወደ አዲስ አበባ የመጡት ኔልሰን ማንዴላ፤ በእስራኤል ሃገር በዉትድርና ትምህርት በሰለጠኑት በዚያን ጊዜዉ መቶ አለቃ ፈቃዱ ዋኬኔ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአራት ሳምንታት ወታደራዊ ስልጠናን አግኝተዋል። ስለ ኮሎኔል ፈቃዱ ዋኬኔ ማንነት የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን በስልክ አጠር ያለ መረጃ ሰጥቶናል።
ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ