የክሩዝ አዲሱ ገጸ-ባህሪ ለጀርመን ታሪክ ጥፋት?
እሑድ፣ ሐምሌ 8 1999ማስታወቂያ
ቶም ክሩዝ ይህን ፊልሙን እንዳይሰራ የታገደበት ምክንያት ምንድን ነዉ የዛሪዉ የባህል መድረካችን በቁጥር አንድ ርእሱ ሊያስቃኘን ተዘጋጅቶአል። ሌላዉ ባለፈዉ ሳምንት የአለም ሰባቱ አስደናቂ ቅርሶች በሚል በሊዝበን ፖርቱጋል ዉስጥ ምርጫ ተካሂዶ ሰባት የአለም ድንቅ ቅርሶች ተመርጠዋል። በዚህ ምርጫ በኢትዮጽያ የሚገኙ ጥንታዊ እና አስደናቂዎቹ አብያተ ክርስትያናት ወይም የአክሱሙ ሃዉልታችን ከሰባቱ ምርጥ የአለም ቅርሳት ለመካተት እድል አላጋጠመዉም። እዉነት ቅርሶቻችን ጥንታዊና ማራኪ ሳይሆኑ ቀርተዉ ነዉን? ባለሞያ አነጋግረናል! ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ