የኬንያ የአትሌቲክስ ባለስልጣናት መታገድ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 21 2008ማስታወቂያ
ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ የኬንያ አትሌቶች የደረሰባቸዉን ጉልበት (ኃይል) ሰጪ መድኃኒት የመጠቀም ክስ በመቃወምና ጉዳዩ በትክክል እንዲመረመር በመጠየቅ ናይሮቢ አትሌቲክስ ዋና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ለቀናት ተቃዉሞ አካሂደዉ እንደነበር። በኬንያ የአትሌቲክስ ጽ/ቤት ቅጽር ግቢ ዉስጥ ተቃዉሞ ካደረጉት መካከል የቀድሞዉ የዓለም ማራቶን ሻንፒዮን እና በአሁኑ ወቅት የኬንያ አትሌቲክስ ማኅበር ሊቀመንበር ዊልሰን ኪፕሳንግ፤ እንዲሁም በጎርጎርዮሳዊ 2012 ዓ,ም የቦስተን ማራቶን አሸናፊ ዊስሊ ኮሪ ይገኙበታል። ከሁለት ወራት በፊት የኬንያ የአትሌትክስ ቢሮ ኃይል ሰጭ መድኃኒት መዉሰዳቸዉ በምርመራ የተረጋገጠ ሁለት ሯጮች ከዉድድር ሜዳ መታገዳቸዉን ይፋ አድርጎም ነበር። የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር፤ የኬንያን የአትሌቲክስ ቢሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለምን ይሆን ያገደዉ፤ እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ ቀደም ሲል የናይሮቢ ወኪላችንን በስልክ ጠይቄዉ ነበር።
ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ