የኬንያ ምርጫ ዉጤትና ዉዝግብ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 10 2009ማስታወቂያ
የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕብረት መሪ ራይላ ኦዲንጋ ባለፈዉ ሳምንት የተደረገዉን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዉጤት ለማሻር በፍርድ ቤት እንደሚሟገቱ አስታወቁ። NASA በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉን የተቃዋሚዎች ሕብረት ወክለዉ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረዉ የነበሩት ኦዲንጋ ባላጋራቸዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ ያሸነፉት የኮምፒዉተር ሰነድን አዛብተዉ ነዉ ባይ ናቸዉ። ፕሬዝደንት ኬንያታ ምርጫዉን በ54 ከመቶ ድምፅ ማሸነፋቸዉን የሐገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል። በተያየዘ ዜና የኬንያ መንግስት፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሐገር በቀል ድርጅቶች እንዲዘጉ ያሳለፈዉን ዉሳኔ ለሰወስት ወራት ያክል አነሳ። ስለ ኬንያ የምርጫ ዉዝግብ የፖለቲካ ተንታኝ ፍቅረማርያምን በሥልክ አነጋግሬያቸዉ ነበር።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ