የካንሰር ችግርና ትኩረት
ሐሙስ፣ የካቲት 24 2003ማስታወቂያ
በዚህ በሽታ የተጠቁ ህፃናት በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደገ ቢሆንም መድሃኒቱ እንደተወደደባቸዉ ነዉ ልጆቻቸዉን የሚያሳክሙ ወላጆች ለዘጋቢያችን የገለፁት። ካንሰር በምርመራ ቶሎ ከታወቀ ለህክምናዉ እንደሚቀል ባለሙያዎች ቢናገሩም አብዛኛን ጊዜ ዘግይወተዉ ወደሃኪም ለሚሄዱ ወገኖች ጥረቱ ተስፋ አስቆራጭ ይመስላል። ባለፈዉ ሰሞን ስለበሽታዉ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የእግር ጉዞ መደረጉም ተገልጿል።
ጌታቸዉ ተድላ
ሂሩት መለሠ