የከብቶች ጤና፤ በአፍሪቃ ቀንድ
ማክሰኞ፣ ጥር 25 2002ማስታወቂያ
በሃኖቨር የእስሳት ህክምና ማሰልጠኛ ተማሪዎች አማካኝነት የተቋቋመዉ መንግስታዊ ያልሆነዉ ይህ ድርጅት በምሥራቅ አፍሪቃ በተለያዩ አገራት የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ህይወት ለማሻሻል፤ የእንስሳቶቻቸዉንም ጤንነት በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከዚህም ሌላ ለአርብቶ አደሮቹ የተሻለ ዉጤት የሚያስገኙ የከብት ዝርያዎችን በማዳቀል የሚያገኙት ጥቅም እንዲሰፋ እየረዳ ነዉ። ሰሞኑን በሰሜናዊ ሶማሊያ ራስ ገዝ ግዛት ፑንትላንድ ከአንድ መቶ ለሚልቁ አርብቶ አደሮች ወተትና አይብ፤ እንዲሁም ስጋቸዉን በገፍ ለመጠቀም የሚያስችሉ ፍየል ዘሮችን አከፋፍሏል።
Sophie Grenery
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ