1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ጥያቄና የአንድ ባለሙያ አስተያየት፧

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 17 1999

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር የተሰኘው ኃይል ከተመሠረተ 23 ዓመት ሲሆነው ገሚስ ምድረ-በዳ የሆነው፧ ምሥራቃዊው የኢትዮጵያ ክል ሰፋ ያለ የውስጥ አስተዳደር መብት ያገኝ ዘንድ የትጥቅ ትግል የሚያካሂድ ንቅናቄ መሆኑ ነው የሚነገርለት።

https://p.dw.com/p/E0aj
በአ.አ. ቦሌ፧ አምቡላንሶች በኦጋዴን የቆሰሉ ቻይናውያንን ለማከም ሲሠማሩ፧
በአ.አ. ቦሌ፧ አምቡላንሶች በኦጋዴን የቆሰሉ ቻይናውያንን ለማከም ሲሠማሩ፧ምስል AP
ይህ የደፈጣ ውጊያ ድርጅት ባለፈው ሚያዝያ፧ በዚያው በኦጋዴን ቻይናውያን በተሠማሩበት የነዳጅ ዘይት ፍለጋ ጣቢያ አደጋ ጥሎ 74 ሰዎች መግደሉ፧ ከዚያም ግንቦት 20 ቀን 1999 ዓ ም ጂጂጋ ላይ ህዝብ በተሰበሰበበት ክብረ-በዓል ላይ የፈንጂ አደጋ ጥሎ የአካባቢውን መስተዳድር ፕሬዚዳንት ማቁሰሉና ጥቂት ሰዎች መግደሉ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት፧ አማጽያኑን ለመቅጣትም ሆነ ከአካባቢው ለማስወጣት ተስፋ በማድረግ አጸፋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደቀጠለ ነው፧ የዜና አውታሮች የሚገልጹት። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ሰው-ሠራሽ የረሃብ ዕልቂት በኦጋዴን ኑዋሪዎች ላይ ተደቅኗል በማለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አጣሪ ቡድን እንዲልክ የተማፀነ ሲሆን፧ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በተለይ ከምሥራቃዊው የአገሪቱ መስተዳድር በኩል እንደተገለጠው ከሆነ የምግብ እጥረት የለም፧ የምግብ እርዳታ ወደዚያ እንዳይላክም አልተከለከለም። ታዛቢዎችም ሆኑ ስለአፍሪቃ የፀጥታ ይዞታ በየቀጣናው የሚመራመሩ ወገኖች ምን ይላሉ? ዋና ጽህፈት ቤቱ በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው የጸጥታ ይዞታ ጥናት ነክ ተ ቋም ከፍተኛ የምርምር ክፍል ባልደረባ Richard Cornwell........
«እዚያው፧ እቦታው ተገኝቶ በዐይን ማየት እስካልተቻለ ድረስ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመግለጽ ከባድ ነው። ኦጋዴኖች፧ ዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ፧ የሆነ እውነት አጣሪ የልዑካን ቡድን አሠማርቶ፧ ከአማጽያኑ አንጻር የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወስደውን አጸፋዊ የእርምጃ ስልት እንዲታዘብ የጠየቁበት ሁኔታ የጉዳዩን ዋና ነጥብ ያነሣ ነው። እርግጥ ነወእ የኢትዮጵያ መንግሥት፧ የግዛት’ ሉዓላዊነትን ክእብር የሚነካ በመሆኑ ጥያቄውን ይቀበለዋል ወይም ይስማማበታል ብሎ ማሰብ የማይቻል ነው። በሌላም በኩል፧ ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ፧ የኢትዮፕያ መንግሥት ጥሩ ነገር አያደርግም የሚል ጥርጣሬ እንዳይኖራቸው፧ መንግሥት አይፈቅድም። ምክንያቱም፧ ሞቀዲሹ ውስጥ፧ በዚያ ያጋጠመውን አመፅ ለማረቅ ኢትዮጵያ ያሰየችው ባህርይ አስወቅሷት ነበረና ነው። የኢትዮፕያ መንግሥት ለተመሳሳይ ነቀፌታ እንደገና በር ይከፍታል ብሎ ማሰብ የማይቻል ነው። ስለዚህ፧ በኦጋዴን ምን እንዳጋጠመ ለማወቅ መጣር በጣም ጠቃሚ ነው። በሌላም በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት በመፍቀድ የሚተባበር አይመስለኝም።«
ታዲያ ምን ይሻላል? ምንድን ነው አብነቱ?
«እምብዛም መፍትኄዎች ያሉ አይመስለኝም። ችግሩ፧ በ CNN (የቴሌቭዥን ድርጅት) የማይታይ እስከሆነ ድረስ፧ ለአብዛኛው የዓለም ህዝብ፧ ምንም እንደሌለ ነገር ነው የሚቆጠረው። የኢትዮጵያ መንግሥትና ሌሎች መንግሥታትምይህን በሚገባ ያውቃሉ። ስለሆነም፧ ይህን የመሰለው ጉዳይ በህዝብ እንዳይታወቅ ወይም እንዳይታይ ነው የተቻላቸውን ሁሉ የሚያደርጉት። ኦጋዴን ደግሞ፧ ሰፊ ግዛት ቢሆንም፧ ራቅ፧ ፈንጠር ብሎ የሚገኝ አካባቢ ነው።«
Richard Cornwell ከዚህ ጋር በማያያዝ፧ «ምናልባትም ሶማልያንና ሶማሊላንድን በሚያዋስነው ድንበር አንዳንድ የሶማልያ አማጽያን ጣልቃ እየገቡ ሊሆን ይችላል፧ ይህ ደግሞ አንዳንድ የዓለም አቀፉ መኅበሰብ አባላት በተለይ ዩናይትድ እስቴትስ አሜሪካ፧ ከራሷ ጥቅም በመነሣት፧ ኢትዮጵያን በመርዳት፧ በዚያ አካባቢ ያለው ሁኔታ እንዳይወሳ ማድረጓ አልቀረም« ይላሉ። ኦጋዴን ውስጥ በአርብቶ-አደርነት የተሠማሩትና ጎስቋላ ህይወት ያላቸው ሲቭሎች አሁን ምን ይበጃቸዋል?
«ኅልውናቸወእእንዲጠበቅ የውጭ እርዳታ የግድ ያስፈልጋቸው። በጦርነት ቀጣና ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ዕድለቢሶች ሆነዋል።አማጽያንና የመንግሥት ወታደሮች በዚህ ዓየቱ ውዝግብ፧በጦርነት ጊዜ የሲቭሉን ህዝብ ደኅንነት ለመተበቅ የተፈረውመውን የጀኔቩን ውል ያከብራሉ ተብሎ አይታሰብም። ይህም ነው እንግዲህ፧ ዓለም አቀፉ ማኅበረ-ሰብ፧ በጥሞና ሁኔታውን መከታተል ያስፈልገዋል የሚባልበት ተጨማሪው ምክንያት!«