የኦባማ ጉብኝትና የአፍሪቃ መርሕ
ረቡዕ፣ ሰኔ 19 2005ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ በሰወስት የአፍሪቃ ሐገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬ ማታ ከዳካር-ሴኔጋል ይጀምራሉ። ኦባማ ሳምንት በሚዘልቅ ጉብኝታቸዉ ከሴኔጋል ሌላ ታንዛኒያንና ደቡብ አፍሪቃን ይጎበኛሉም። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ያነጋገራቸዉ አፍሪቃ-አሜሪካዉያንና አንድ አሜሪካዊ ዲፕሎማት እንደሚሉት ኦባማ በመጀመሪያዉ ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ለአፍሪቃ ብዙም ትኩረት አልሰጡም ነበር። አስተያየት ሠጪዎቹ እንደሚያምኑት ከኬኒያዊ አባት የሚወለዱት አሜሪካዊዉ ፕሬዝዳት አሁኑ አፍሪቃን መጎብኘታቸዉ ሥለ አፍሪቃ የሚከተሉትን መርሕ ለማጠናከር አስበዉ ሳይሆን አይቀርም።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ