1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሕዝብ አስተያየት

ዓርብ፣ ሐምሌ 17 2007

ኬንያ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማን ለመቀበል የፀጥታና የደህንነት ይዞታዋን በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከሯ እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1G4KD
Barack Obama Iran Nuclear Vertrag Einigung Atom Deal
ምስል picture-alliance/EPA/A. Harnik

[No title]

ዋና ዋና መንገዶች ለጊዜዉ እንደሚዘጉ የገለፁት ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያዉም እንዲሁ እሳቸዉን የያዘዉ አዉሮፕላን ሲደርስም ሆነ የኬንያ ጉብኝታቸዉን ፈፅመዉ ወደ ኢትዮጵያ በሚጓዙበት ሰዓትም እንደሚዘጋ ገልጸዋል። ሳፋሪኮም የተሰኘዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅትም በኦባማ ቆይታ ወቅት አገልግሎቱ ችግር ሊገጥመዉ እንደሚችል ከወዲሁ ለደንበኞቹ ጠቁሟል። ናይሮቢ ላይ በሚካሄደዉ የንግድ ጉባኤ የሚገኙት ኦባማ እሁድ ዕለት ወደኢትዮጵያ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት አስመልክቶ የሕዝብ አስተያየት አሰባስበናል።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ