የኦባማ ና የኔታንያሁ ውይይት
ረቡዕ፣ የካቲት 28 2004ከዩናይትድ ስቴስትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ትናንት ዋሽንግተን ውስጥ የተነጋገሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚንኔታንያሁ ሃገራቸው እስካሁን የኢራን የኒዩክልየር ተቋማትን የማጥቃት ውሳኔ ላይ አለመድረሷን አስታወቁ ። ሆኖም ነታንያሁ እስራኤል ፣ ራስዋን በወታደራዊ እርምጃ ከጥቃት የመከላከል ውሳኔ ላይ የመድረስ መብትዋን ለወደፊቱ እንደያዘችው ተናግረዋል ። ኦባማ በበኩላቸው በኢራን ላይ ማዕቀቦችን ከመጣል ይልቅ ለዲፕሎማሲው ጥረት ይበልጥ ጊዜ እንዲስጥ አሳስበዋል ።እስራኤል ግን በኢራን የኒዩክልየር መርሃ ግብር ሰበብ የተነሳውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ መፈታት መቻሉን ትጠራጠራለች ። ክላውስ ካስታን ያቀረበውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለችዩናይትድ ስቴትስም ሆነች እስራኤል የቴህራን መሪዎች የአቶም ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳይሆኑ መግታት ነው ፍላጎታቸው ። ይህ ግን እንደፈለጉት ሊሰምር አልቻልም ። ቢሆንም በትናንቱ መግለጫቸው ይህን ብዙም አጉልተው አላወጡትም ። ከዚያ ይልቅ ግንኙነታቸው በጥብቅ መሠረት ላይ የቆመ ወዳጅንታቸውም የጠነከረ መሆኑ ላይ ነበር ያተኮሩት ። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሃገራቸው ለእስራኤል ደህንነት ያላትን ቁርጥኝነት ዳግም አረጋግጠዋል ።
« የእሰራኤልን ደህንነት ለማስከበር ያለን ቁርጠኝነት ፍፁም የጠጠረ ነው ።
ነተንያሁ ድግሞ በምላሹ አሜሪካንና እስራኤል እንድም ሁለትም መሆናቸውን መሰከሩ ።
«እኛ እናንተ ነን ። እናንተ ደግሞ እኛ ናችሁ ። አንድ ላይ ነን ።
የዩናይትድ ስቴስትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ ትናንት ዋሽንግተን ውስጥ ያካሄዱት ውይይት ልዪ ትኩረት በኢራን የኒዩክልየር መርሃ ግብር ላይ እስራኤል ያደርባት ስጋት ነበር ። ኢራን የኒዩክልይር ጦር መሣሪያዎች ባለቤት ለመሆን አላት የሚባለው ጉጉትና የኢራን መሪዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት እስራኤል ከዓለም ካርታ መጥፋት አለበት ሲሉ መዛታቸው ፣ኢራን እስራኤል ለህልውናዋ እጅግ አስጊ አደርጋ የምትቆጥራት ሃገር ናት ። ነተንያሁ ትናንት እንዳስታወቁት እስራኤል በህልውናዋ በመጣ ጉዳይ ላይ አትደራደርም ። ራስዋን የመከላከል እርምጅዎችንም ከመወሰድ ወደ ኋላ አትልም
« የእስራኤልን ደህነንት በሚመለከት ፣ እስራኤል የራስዋን እርምጃዎች የመወሰድ ሉዓላዊ መበት እላት »
ምንም እንኳን እስካሁን አንድም የእስራኤል መሪ ኢራንን ለማጥቃት በይፋ ማስጠንቀቂያ ባይናገርም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ይህን መሰሉ እርምጃ እንዲወስድ ፈቃድ የመገኝቱ ጭምጭምታ ሲሰማ ነበር የከረመው ። ይሁንን ክኦባማ ና ክንትንያሁ ንግግር በኋላ እስራኤል አሰቀድማ ይዛላቸ በተባለው እቅዷ መሠረት በኢራን የኒዩክልየር ተቋማት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ አለመውሰዷ በግልጽ አልታወቀም ። ባራክ ኦባማ ግን ወታደራዊ እርምጃ መወሰዱን እስካሁን ድረስ አይቀበሉም ። ክዚያ ይልቅ ሌሎች አማራጮች ይሞከሩ ነው የሚሉት ። ባለፈው እሁድ በዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኢል ድጋፍ በማሰባሰብ በሚታወቀው በእንግሊዘኛው ምህፃር AIPAC በተባለው ድርጅት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ኢራን የኒዩክልየር ቦምብ ባለቤት እንዳትሆን ሃገራቸው ያሉትን አማራጮች ሁሉ ክፍት አንደምታደርግ አሰታውቀው ነበር ። ኦባማ በኢራን ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በመጪዎቹ ወራቶች የሚያመጡትን ወጤት እንጠብቅ ነው የሚሉት ። በምንም ዓይነት መንገድ ሃገራቸው ሌላ ጦርነት ወሰጥ እንድትገባ እንደማይፈልጉ ነው ያሳውቁት ። ትናንት ከነታንያሁ ጋር ከተወያዩ በኋላም ከቴህራን ጋር ስላለው ውዝግብ ሲያውሱ ዲፕሎማሲ የሚልውን ቃል ሶስት ጊዜ አንስተዋል ።
« አሁንም ለጉዳዩ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ የሚያስገኝ ተስፋ አለ ። ሆኖም በሰተመጨረሻ የኢራንን አገዛዝም በዚህ አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ እስካሁን ያላደረገው ውሳኔ ላይ መድረሰ አለበት ። »
ለኦባማ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንዳሉት ኦባማ የእስራኤሉ እንግዳቸው በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃዎች ከመውሰድ እንዲቆጠቡ አበክረው መክረዋል ። ኦባማ እስራኤል በአሁኑ ሰዓት ኢራንን እንዳትመታ የጠየቁት በምትኩ ለእስራኤል ምን ለማድረግ አስበው ይሆን የሚሉ ወገኖች አሉ ታዛቢዎች እንደሚሉትእስራኤል የአሜሪካንን ጥያቄ የምትቀበል ከሆነ በምትኩ ደግሞ ከዋሽንግተን የሆነ ነገር ትቀበላለች ። ምናልባት ዲፕሎማሲውም ማዕቀቡም አልሰራ ብሎ ወደ ወታደራዊ አርምጃ የሚገባ ከሆነ እርምጃ የምትወስደው እስራኤል ብቻ ሳትሆን አሜሪካ ጭምር ልትሆን ትችላለች የሚል ማካካሻ ለእስራኤል ቃል ሳይገባላት አይቀርም ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ