የኦሮምያ ክልል ዕቅድና ትችቱ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 7 2008ማስታወቂያ
የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከ832 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር ያወጣው እቅድ እያነጋገረ ነው። የክልሉ መንግሥት እንደሚለው እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ 2.4 ቢሊዮን ብር ተመድቧል። የመጀመሪያውን ዙር ሥራ በተግባር ለመተርጎም 300 ሚሊዮን ብር ተመድቦ እንቅስቃሴ መጀመሩን የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ለዶቼቬለ አስታውቋል። ኃላፊው እንዳሉት የዕቅዱ ይዘትና አተገባበር ላያ ያተኮረ ሥልጠናም ለወጣቱ እየተሰጠ ነው። ዕቅዱ የተለጠጠ እና ለፖለቲካ ፍጆታ የታሰበ ነው የሚሉ ትችቶች እየተሰነዘሩበት ነው። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ