1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእናቶች ቀን

ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2003

በሚያዝያ ወር መዳረሻ ጀምሮ ያሉት ሶስት እና አራት ወራቶች ጀርመናዉያን በጉጉት የሚጠብቋቸዉ የሚወዱዋቸዉ ወራቶች ናቸዉ። በሚያዝያ ወር ሲዳረስ የሚያንዘፈዝፈዉ ብርድ ተጠናቆ ጸሃይ የሙቀት ጮራዋን የምትፈነጥቅበት

https://p.dw.com/p/RNX3
እናትና ልጅ ጣና ሐይቅ ላይምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

በክረምቱ ብርድ ቅጠሉ ረግፎ ርቃኑን ቆሞ የነበረዉ ዛፍም፣ ቅጠል ዳግም አዉጥቶ አገሪቷን በአረንጓዴ ቀለሙ የሚያደምቅበት፣ አበቦች የሚያብቡበት ግዜ ነዉ። በሚያዝያ ወር የአየሩ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን መለወጥ የሚጀምረዉ በክረምቱ ወራት ተኮሳትሮ ይታይ የነበረዉ ነዋሪ ደራርቦት የቆየዉን ካፖርታ አዉጥቶ ጥሎ ሳሳ ባለች ሸሚዝ በፈገግታ ፊቱን ቀይሮ ወጣ የሚልበት ልጃገረዶችም አጠር አጠር ያለ ቀሚሳቸዉን አድርገዉ የሰዉንነት ቅርጽ ዉድድር የጀመሩ የሚመስልበትም ወር ነዉ። ይህንኑ የአየር መሞቅ የበጋ ወራት መግባትን ተከትሎ ጀርመናዉያን ማህበረሰብን የሚያሰባስብ አካባቢያዊ አገር አቀፍ፣ ከዝያም አልፎ አለም አቀፍ የተለያዩ አዝናኝ እና ትምህርታዊ መድረኮችን ይከፍታሉ።
በመጭዉ ቅዳሜ ምሽት የአዉሮጻ አገሮች የሙዚቃ ዉድድር እዚህ የኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት ዋና መዲና በሆነዉ በዲስልዶርፍ ከተማ ይካሄዳል። 43 የአዉሮጻ አገራት ለቅዳሜዉ የዉድድር መድረክ ለመቅረብ የመጀመርያዉን የማጣርያ ዉድድር ባለፈዉ ማክሰኞ አድርገዋል። ሁለተኛዉ የማጣርያ ዉድድርም ዛሪ ምሽት ይካሄዳል። በሚቀጥለዉ ሳምንት ዝግጅታችን የአዉሮጻ አገራት የሙዚቃ ዉድድርን በተመለከተ ሰፋ ያለ መሰናዶአችንን ይዘን እንቀርባለን። ምዕራባዉያን በየአመቱ የአዉሮጻዉያኑ የሚያዝያ ወር በገባ ሁለተኛዉ ሳምንት እሁድ በድምቀት የሚያከብሩትን የእናቶች ቀን ታስቦዉሎአል። ዘንድሮ ይህ የእናቶች ቀን በኢትዮጽያዉያን አቆጣጠር ሚያዝያ ሰላሳ ነበር የዋለዉ። በለቱ ዝግጅታችን ጀርመናዉያን አለም አቀፍን የእናቶች ቀን እንዴት ያከብራሉ በሚል ጀምረን በአገራች የእናቶች ቀን በተመከተ ዉይይት አድርገን ጥንቅር ይዘናል ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ