1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነ አቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ግንቦት 30 2009

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ የጸረ-ሽብር ሕግ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ሆን ብሎ የፍትኅ ሒደቱን እያጓተተ ነው ሲሉ አማረሩ።

https://p.dw.com/p/2eHUp
Äthiopien Politiker Bekele Gerba
ምስል Addis Standard Magazine

Ber. Addis Ababa -Gurmessa Ayano et al /Bekele Gerba court hearing - MP3-Stereo

ከተከሳሾቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ቡላላ ለፍርድ ቤቱ "መጉላላቱ አግባብነት የለውም። ከእናንተ ጀርባ የደኅንነት እጅ እንዳለ ይገባናል። እያከናወናችሁት ባሉት ተግባራት እናንተንም አገራችንንም እንድንጠላ እያደረጋችሁን ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲግ ኮርፖሬሽን(ኢቢሲ) ተተርጉሞ በሚቀርበው ሰነድ ላይ ተመርኩዞ ብይን ለመስጠት ለዛሬ የሰጠውን ቀጠሮ እንደገና ለአምስተኛ ጊዜ አራዝሞታል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

እሸቴ በቀለ