የእነ ሃብታሙ አያሌው የፍርድ ቤት ውሎ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ሃብታሙ አያሌው መዝገብ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ይግባኝ ዛሬ አዳመጠ። ፓርቲያቸውን ሽፋን በማድረግ ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ለመናድ በማሴር የተከሰሱትን ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር በፊት የታሰሩትን 4 የአንድነት የሰማያዊ እና የአረና ትግራይ ፓርቲ አባላት ጉዳይ ከዚህ ቀደም የተመለከተው ፍርድ ቤት በነፃ እንዲሰናበቱ ቢወሰንላቸውም አቃቤ ህግ ውሳኔው እንዲታደግ ያቀረበውን አቤቱታ ነበር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ያዳመጠው ።ችሎቱ በ4ቱ ፖለቲከኞች ጉዳይ ላይ የቀረበውን ይግባኝ መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ