የእስራኤል ጦር ከጋዛ መውጣቱና የአረብ ሊግ
ሰኞ፣ ጥር 11 2001ማስታወቂያ
የእስራኤል ጦር ትናንትና ማታና ዛሬ ማለዳ ከጋዛ መውጣት መጀመሩ ተገለፀ። ጋዛ በሶስት ሳምንቱ የቦንብ ጥቃት በትንሹ ሃያ ሁለት ሺህ የሚጠጉ የግልና የመንግስት ህንፃዎቿ የተጎዱ አለያም የተደረመሱ መሆናቸውን DPA የፍልስጥኤም ማዕከላዊ የመረጃ ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል። ዛሬ ኩዌት ውስጥ በተጀመረው የአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ደግሞ፤ የኩዌቱ አሚር ሼክ ሳባህ “እስራኤል የጦር ወንጀለኛ ናት” ሲሉ፣ የሶሪያው ፕሬዚዳንት ባሽር አል አሳድ “እስራኤል በአሸባሪ መዝገብ ውስጥ መስፈር አለባት” ሲሉ ተናግረዋል። ጉባኤው እስራኤልን በተመለከተ ልዩነት እንደነበረበትም ተጠቅሷል።