1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2005

በቦምብ የተደበደበውን የጋዛ ክፍል የጎበኙትና ዛሬ በተፈፀመ ጥቃት ተገድለዋል የተባሉትን ሰዎች አስከሬን ያዪት ካንዲል የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲፀናና እስራኤልም ጥቃቱን እንድታቆም ግብፅ ጥረቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/16kjk
Palestinians extinguish a fire after Israeli air strikes targeted Interior Ministry building in Gaza City, on November 16, 2012 . AFP PHOTO/MAHMUD HAMS (Photo credit should read MAHMUD HAMS/AFP/Getty Images)
Israel Angriffe auf Gazaምስል Mahmud Hams/AFP/Getty Images)

እስራኤል በጋዛ የምትሰነዝረውን ጥቃት እንዲያስቆሙ የአለም መንግሥታት ተጠየቁ ። ዛሬ በጋዛ አጭር ጉብኝት ያደረጉት የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሺም ካንዲል የአለም መንግሥታት እስራኤልን አንድ እንዲሉ ተማፅነዋል ። በቦምብ የተደበደበውን የጋዛ ክፍል የጎበኙትና ዛሬ በተፈፀመ ጥቃት ተገድለዋል የተባሉትን ሰዎች አስከሬን ያዪት ካንዲል የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲፀናና እስራኤልም ጥቃቱን እንድታቆም ግብፅ ጥረቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል ። በካንዲል የጋዛ ጉብኝት ወቅት ስምምነት ላይ የተደረሰበት ተኩስ አቁም ወዲያውኑ ተጥሶ ሰሜን ጋዛ ውስጥ በተፈፀመ የእስራኤል የአየር ጥቃት 2 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል ። ሆኖም ሃማስን ስምምነቱን በመጣስ የወነጀለችው እስራኤል ዛሬ የአየር ጥቃት አልፈፀምኩም ብላለች ። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ከ60 በላይ ጓዳ ሰራሽ ሮኬቶች ወደ እስራኤል እንደተተኮሱ ተናግረዋል ። ሃምስ በበኩሉ 40 ሮኬቶች መተኮሳቸውን አምኗል ። እስራኤል ዘመቻዋን

Smoke rises after Israeli air strikes in Gaza City November 16, 2012. Egypt's prime minister prepared to visit the Gaza Strip on Friday in an unprecedented display of solidarity with Hamas militants embroiled in a new escalation of conflict with Israel that risks spiralling into all-out war. REUTERS/Ahmed Zakot (GAZA - Tags: CIVIL UNREST MILITARY POLITICS)
ምስል Reuters

በማጠናከር 16 ሺህ ተጠባባቂ ወታደሮቿን ጠርታለች ። የእስራኤል ካቢኔ አባል ሞሼ ያሎን መንግሥታቸው የሚሰነዘረውን የሮኬት ጥቃት ከነአካቴው ለማስቀረት እግረኛ ጦሯን ለማዝመት እያሰላሰለ መሆኑን ተናግረዋል ። የአውሮፓ ህብረት ሃማስን አውግዞ የእስራኤልም እርምጃም ተመጣጣኝ እንዲሆን ጥሬ አቅርቧል ። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ካትሬን አሽተን ሃማስና ሌሎችም ቡድኖች ወደ እስራኤል ሮኬቶች መተኮሳቸው ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀው መቆም አለበትም ብለዋል ። ህዝቧን ከጥቃት የመከላከል መብት አላት ያሏት እስራኤልም የምትወስደው እርማጃ ተመጣጣኝ እንዲሆን ጠይቀዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ