1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል - ጋዛ ግጭት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2006

የጋዛ ግጭት ውዝግቡ ካለፈው አንድ ሳምንት ወዲህ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፣ ፍልሥጤማውያን ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን፣ የእስራኤል ጦርም ጋዛን ማጥቃታቸውን ቀጥለዋል። በዚሁ መሀል እስራኤል እና

https://p.dw.com/p/1Cdc5
Palästina Israel Luftangriff auf den Gazastreifen 13.07.2014
ምስል Reuters

ሀማስ የኃይሉን ተግባር እንዲያቆሙ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረትሁለቱን ተቀናቃኝ ወገኖች ወደ ድርድሩ ያመጣቸው ይሆናል በሚል ብዙዎች አሳድረውት የነበረው ተስፋ መና መቅረቱ ተሰምቶዋል። ግብፅ ትናንት ለሁለቱ ያቀረበችውን የተኩስ አቁም ሀሳብ እስራኤል ስትቀበለው፣ ሀማስ ግን ገና ሀሳቡን እያጠና መሆኑን ነው ያስታወቀው።

ጋዛን ከእስራኤል ጋ ከሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ዛሬ ከቀትር በፊት ወደ እስራኤል ሮኬቶች መተኮሳቸው ተሰምቶዋል። የፍልሥጤማውያን የምክር ቤት አንጃ የተኩስ አቁም ደንብ ለመድረስ ባለፉት ቀናት ዝግጁነቱን አሳይቶ ነበር፤ ይሁንና፣ የሀማስ ድርጅት ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው፣ ትናንት ከግብፅ የቀረበው የተኩስ አቁም ደንብ ሀሳብ ያልጠበቁት ነበር

« እኛን ማንም አላነጋገረንም። ሀሳቡን ከመገናኛ ብዙኃን ነው የሰማነው። ውዝግቡን ለማብቃት የሚደረግ ማንኛውንም ጥረት እንደግፋለን፤ ግን፣ ካይሮ ከኛ ጋ ቀጥተኛ ውይይት እንዲያካሂድ እንጠይቃለን። በቀረበው ሀሳብ ላይ ከተመካከርን በኋላ አቋማችንን፣ እንዲሁም፣ መደረግ አለባቸው የምንላቸውንም የለውጥ ሀሳቦች እናሳውቃለን። »

Benjamin Netanyahu und Frank-Walter Steinmeier Tel Aviv Israel
ምስል Reuters

የእስራኤል ጦር ጥቃቱን ማቆሙን ቢያስታውቅም፣ የፈረንሳይ ዜና ወኪል እና ያይን ምስክሮች እንዳሉት፣ የእስራኤል ተዋጊ አይሮፕላኖች እንደገና ጥቃታቸውን በመጀመር ዛሬ ጋዛን ቢያንስ አራት ጊዜ ደብድበዋል። የግብፅን ሀሳብ ከእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን እና ከኤኮኖሚ ሚንስትር ናፍታሊ በስተቀር ጠቅላላ የሀገሪቱ ፀጥታ ካቢኔ አባላት ተቀብለውታል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ይህንን ለሽምግልና ወደ እስራኤል ለተጓዙት የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር አረጋግጠዋል።

« ጋዛ ሠርጥን በፖለቲካዊው መንገድ ከጦር መሳሪያ ትጥቅ ለማላቀቅ ግብፅ ያቀረበችውን ሀሳብ ደግፈነዋል፣ ነገር ግን፣ ሀማስ የተኩስ አቁም ደንብ ለመድረስ የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ ካደረገው ያኔ እስራኤል ፀጥታዋን ለማስከበር ወታደራዊውን ርምጃ እንደገና የመጀመር መብት አላት። »።

ጀርመናዊው ውጭ ጉዳይ ሚንስትርም የሀገራቸውን ድጋፍ ለኔታንያሁ ገልጸዋል።

Bildergalerie Kinder in Gaza und Israel
ምስል Mahmud Hams/AFP/Getty Images

በተለይ ከጋዛ ጋ በሚዋሰነው ደቡባዊ እስራኤል ባሉ አሽኬሎንን በመሳሰሉ ከተሞች የሚገኙ እንደ ሪሞና ያሉ ነዋሪዎች የተኩስ አቁሙን ሀሳብ ተቃውመውታል።

« ካለ ተኩስ አቁም ደንብ ወደ መደበኛው ኑሯችን መመለስ እንፈልጋለን። የጥቃቱ ዘመቻ እንዲቀጥል እንፈልጋለን። »

በእስራኤል የጥቃት ዘመቻ የተነሳ አካባቢውን እየለቀቀ መሸሽ የተገደደው በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖረው በተለይ ጥቃቱ ዋነኛ ዒላማ ያደረጋት የቤት ላህያ ከተማም ሕዝብ ሁኔታው እንዳስመረው ነው የገለጸው።

« እየተፈጸመ ያለውን ተመልከቱ፣ ኑሯችን ምን ያህል አዳጋች እንደሆነ። አንዱ ጥቃታ ሲያበቃ ሌላው ይከተላል። አይሁዳውያኑ ለምንድን ነው በቦምብ የሚደበድቡን? እንዴት እንደሚቀጥል አናውቅም። »

በሰባት ቀኑ የእስራኤል ጥቃት 184 ሰዎች ተገድለዋል፣ ከ1,200 የሚበልጡ ቆስለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩም ተፈናቅለዋል።

ቤቲና ማርክስ/አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ