የእስራኤል ድብደባ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 22 2006ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋዛ ሰርጥ የተጀመረው ጦርነት ገና እንደሚቀጥል ለሀገራቸው ሕዝብ አረጋግጠዋል። እንደ ኔታንያሁ ጦርነቱ የሚያበቃው የእስራኤል ጦር ሀማስ የሰራቸውን የምድር ምሽጎች ሙሉ በሙሉ አፈራርሶ ሲያበቃ ይመስላል። እስራኤል ከሶስት ሳምንት ገደማ በፊት በጋዛ ሰርጥ ጥቃት የጀመረችው ሀማስ ከጋዛ የሚተኩስባትን ሮኬት ለመከላከል በሚል ምክንያት ነው። ከአየር የተጀመረው የእስራኤል ጥቃት አሁን በምድር ጦሯ እና በባህር ኃይሏም ተጠናክሮዋል። ኃይፋ የሚገኘው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ግርማው አሻግሬ
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ