የእስራኤል የጋዛ ድብደባ መቆም
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 29 2006ማስታወቂያ
እስራኤል በጋዛ ለ4 ሳምንታት ያካሄደችውን ድብደባ ዛሬ ጋብ አድርጋ የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም አውጃለች ። የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች ዛሬ ጋዛን ለቀው እስራኤል ድንበር ላይ ሰፍረዋል። ሆኖም የእስራኤል ጦር ለሚሰነዘርበት ማናቸውም ጥቃት የአፀፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ። የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ ከመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊዎች ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሰው ነበር ። ላለፉት 28 ቀናት በተካሄደው ድብደባ ቤታቸው ታስረው የቆዩት ፍልስጤማውያንም ዛሬ መንገዶችንና ገበያዎችን ሞልተው ታይተዋል ። ዛሬ ተግባራዊ ስለሆነው የተኩስ አቁምና ተግባራዊነቱ እንዲሁም ስለ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሃይፋውን ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ