የእስራኤል የአየር ጥቃት ቁጣ አስነሳ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 21 2001ማስታወቂያ
እስራኤል ከጦር እውሮፕላኖቿ በምታዘንበው የቦንብ ጥቃት የፍልስጥኤሟ ጋዛን ስትደበድብ አራተኛ ቀኗ መዳረሱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ። የሟቾቹ ቁጥር በትንሹ ሶስት መቶ ስልሳ ደርሷል። ጥቃቱ በበርካታ የአረብ አገራት ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል። እስራኤል ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሶ የሮኬት ጥቃቶችን በማድረስ ስለተዳፈረኝ ለሳምንታት የሚዘልቀው የአየር ጥቃት ገና በምድርም ይቀጥላል ስትል ገልፃለች።