1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል እርምጃና ተቃዉሞዉ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 30 2006

የእስራኤል መንግሥት ሥደተኞቹን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለአንድ ዓመት ለማሳር ማቀደኑን እና በአስቸጋሪ ሥፍራ በተቋቋሙ ጣቢያዎች ያለፍቃዳቸዉ ማስፈሩን ሥደተኞቹ እና ደጋፊዎቻቸዉ አጥብቀዉ ይቃወሙታል

https://p.dw.com/p/1An88
ምስል Reuters



የእስራኤል መንግሥት ወደ ሐገሩ በገቡ አፍሪቃዉያን ስደተኞች ላይ የሚያደርሰዉን በደል በመቃወም ሥደተኞችና ደጋፊዎቻቸዉ የሚያደርጉት የአደባባይ ሠልፍ ዛሬም ለሰወስተኛ ቀን እንደቀጠለ ነዉ።የእስራኤል መንግሥት ሥደተኞቹን ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለአንድ ዓመት ለማሳር ማቀደኑን እና በአስቸጋሪ ሥፍራ በተቋቋሙ ጣቢያዎች ያለፍቃዳቸዉ ማስፈሩን ሥደተኞቹ እና ደጋፊዎቻቸዉ አጥብቀዉ ይቃወሙታል።ስደተኞቹ እና የመብት ተሟጋቾቹ ካለፈዉ ዕሁድ ጀምረዉ ቴል አቪቭ እና እየሩሳሌም በሚገኙ የዉጪ ኤምባሲያዎች፥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፅሕፈት ቤት፥ እና በእስራኤል መንግሥት መስሪያ ቤቶች ፊትለፊት ተገኝተዉ ተቃዉሟቸዉን እያሰሙ ነዉ።የሐይፋዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ አጭር ዘገባ ልኮልናል።

ግርማዉ አሻግሬ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ