1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ኤምባሲዎች ሠራተኞች አድማ

ዓርብ፣ መጋቢት 19 2006

የአድማው መንስኤ እነዚሁ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኖች ያቀረቡት የደሞዝ ጭማሪ ና የሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጥያቄ መልስ አለማግኘቱ ነው ። ሠራተኞቹ ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ እነዚህን ጥያቄዎች ሲያቀርቡ ቆይተዋል ።

https://p.dw.com/p/1BY8v
Israel Altstadt von Nazareth
ምስል picture-alliance/Arco

በመላው ዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎች ሠራተኞች የመቱት የሥራ ማቆም አድማ ከእስራኤል በሚወጡና ወደ እስራኤል በሚሄዱ መንገደኞች እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ እያደረገ ነው ። ካለፈው እሁድ አንስቶ ላላተወሰነ ጊዜ በመካሄድ ላይ ያለው ይኽው የሥራ ማቆም አድማ በእስራኤል ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሯል ። የአድማው መንስኤ እነዚሁ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኖች ያቀረቡት የደሞዝ ጭማሪ ና የሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጥያቄ መልስ አለማግኘቱ ነው ። ሠራተኞቹ ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ እነዚህን ጥያቄዎች ሲያቀርቡ ቆይተዋል ። ባለፉት ሰባት ወራት ወራት በጉዳዩ ላይ ከአስራኤል የገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ድርድሮች ቢካሄዱም ባለፈው የካቲት 25 2006 ዓም ያለ ውጤት አብቅቷል ። ስለ ሥራ ማቆም አድማውና ተፅእኖው የሃይፋ እስራኤል ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ግርማው አሻግሬ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ