1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል አሰሳና ፍልስጤማውያን

ሰኞ፣ ሰኔ 16 2006

እገታውና በተከታታይ የቀጠለው እስር ሃማስና የፍልስጤማውያን ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ በተፈራረሙት የአንድነት ስምምነት ላይ ተፅእኖ በማድረግ ላይ መሆኑ ተዘግቧል ።

https://p.dw.com/p/1COZQ
Israelische Militäraktion im Westjordanland
ምስል Reuters

እስራኤል የደረሱበት ባልታወቀው ሶስት እስራኤላውያን ተማሪዎች ፍለጋ ምክንያት በፍልስጤም ምድር የጀመረችውን አሰሳ አሁንም አጠናክራ ቀጥላለች ። ትናንት ለሊት በጀኒን ና በሄብሮን በተካሄደ አሰሳ 37 ተጠርጣሪ ፍልስጤማውያን ታስረዋል ።በዚሁ ዘመቻ የእስራኤል ወታደሮች ቤተልሄምና ናብሉስም መግባታቸው ተገልጿል ። እገታውና በተከታታይ የቀጠለው እስር ሃማስና የፍልስጤማውያን ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ በተፈራረሙት የአንድነት ስምምነት ላይ ተፅእኖ በማድረግ ላይ መሆኑ ተዘግቧል ።ከእገታው በኋላ እስራኤል በአንዳንድ ኬላዎች ጥብቅ ቁጥጥር ማካሄዷና አንዳንዴም መዝጋትዋ እንቅስቃሴዎችን አውኳል ። በእርምጃው የሰዎች ህይወት መጥፋቱን በርካታ ሰዎችም መታሰራቸው እስራኤልን በመብት ጥሰት እያስወቀሳት ነው ። ስለ ቀጠለው የእስራኤል እርምጃ የሃይፋውን ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ግርማው አሻግሬ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ