የእስራኤል ሠፈራ መንደርና የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2004ማስታወቂያ
እስራኤል በሐይል በያዘችዉ የምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ካስገነባቻቸዉ የአሁድ ሠፈራ መንደሮች አንዱ እንዲፈርስ የሐገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስኗል።ዉሳኔዉን የእስራኤል የግራ ፖለቲከኞች፥ የሠላም ተሟጋቾችና ፍልስጤሞች ሲደግፉት የእስራኤል ቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞች ግን ተቃዉመዉታል።የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት የእስራኤል መንግሥት በሐይል በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ይፈፀማል ያለዉን ሰብአዊ መብት ረገጣ ለማጣራት ጠይቆ ነበር። እስራኤል አለም አቀፉን ድርጅት ጥያቄ ዉድቅ አድርጋዋለች።ከድርጅቱ ጋር ያላትን ትብብርም አቋርጣለች።ሥለ ሁለቱም ጉዳዩች የሐይፋዉን ወኪላችንን ግርማዉ አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዋለሁ። የመጀመሪያ ጥያቄዬ፥-ፍርድ ቤቱ እንዲፈርስ የበየነበት ሠፈራ መንደር የሚገኝበትንና ዉሳኔዉ ያስከተለዉን ፖለቲካዊ ልዩነት የሚመለከት ነበር።
ግርማዉ አሻግሬ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ