1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስልምና ሥነ-ፅሁፍ በአፍሪቃ ቀንድ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 9 2006

የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ በሚነገሩ በተለያ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶች ሲስጥ እንደነበር አጥኚቹ ተናግረዋል።በተለይ ሐረር ከተማ የገኙ መዛግብትና መፃሐፍት የምሥራቅ አፍሪቃዉ ጥንታዊዉ የሙስሊሞች ሥልጣኔ ከዝነኛዋ የቲምቡክቱ (ማሊ) ሥልጣኔ ጋር ታሪካዊ ትስስር እንዳለዉ ተመራማሪዎቹ አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/1BReH
ምስል Azeb Tadesse Hahn

የኢትዮጵያንና በአካባቢዉ የሚገኙ ሐገራትን የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍን ይዘትና ታሪካዊ ፋይዳዉን የሚቃኝ ዓለም አቀፍ ጥናታዊ ጉባኤ አዲስ አበባ ዉስጥ በመካሔድ ላይ ነዉ።የፈረንሳይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ጥናት ተቋም ከኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ጋር በመሆን በጋራ ባዘጋጁት ጉባኤ ላይ በምሥራቅ አፍሪቃ ሙሥሊሞችና በእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ ላይ ጥናት ያደረጉ የተለያዩ ሐገራት ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፋቸዉን ያቀርባሉ።የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ በሚነገሩ በተለያ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶች ሲስጥ እንደነበር አጥኚቹ ተናግረዋል።በተለይ ሐረር ከተማ የገኙ መዛግብትና መፃሐፍት የምሥራቅ አፍሪቃዉ ጥንታዊዉ የሙስሊሞች ሥልጣኔ ከዝነኛዋ የቲምቡክቱ (ማሊ) ሥልጣኔ ጋር ታሪካዊ ትስስር እንዳለዉ ተመራማሪዎቹ አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ