የእስልምና ሀይማኖት በጀርመን
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 2 2003ማስታወቂያ
ከአንድ ሳምንት በፊት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ክርስቲያን ቩልፍ በጀርመን ውህደት በዓል ላይ የእስልምና ሀይማኖት በጀርመን ውስጥ ቦታ አለው ሲሉ ያሰሙት ይህ ንግግር ከሳምንት በላይ ጀርመናውያን ፖለቲከኞችንና ህብረተሰቡን ሲያነጋግር ከርሟል ። እንደተመረጡ በጀርመን የውጭ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር ይበልጥ እንዲዋሀዱ ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ቩልፍ ከሶስት ወራት የስልጣን ዘመናቸው በኃላ ያስተላለፉት ይህ መልዕክት ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞችንና ለሙስሊሞች ትኩረት መሰጠቱን የሚደግፉትን ሲያስደስት ከፓርቲያቸው አንዳንድ አባላት በኩል ደግሞ ተቃውሞ አስከትሏል ።
ሂሩት መለሠ
ሸዋዬ ለገሠ