1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርዳታ ድርጅቶች ጥሪ ለሶማልያ

ረቡዕ፣ መጋቢት 17 2000

በዛሪዉ እለት 40 ያህል የርዳታ ድርጅቶች፣ በጦርነት ፣ በምግብ እጥረት፣ በድርቅ፣ እንዲሁም በሰባዊ ቀዉስ ዉስጥ ያለችዉን ሶማልያ የአለም ህዝብ ትኩረት እንዲጥል ጥሪ ማቅረባቸዉን የብሪታንያዉ ግብረሰናይ ድርጅት ኦክስፋም አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/E0Xn
ምስል AP Graphics

እንደ ኦክስፋም ገለጻ አንድ ሚሊዮን ሶማልያዉያን በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል። አዜብ ታደሰ በአፍሪቃዉ ቀንድ አካባቢ የ̎ Oxfam ከፍተኛ ባለስልጣን ሚስ Verity Johnson ን አነጋግራ ይህን አጠናቅራለች