1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእሥራኤሉ ምርጫና ጀርመን፤

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2005

እሥራኤል ውስጥ ዛሬ የፓርላማ ምርጫ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፤ በህዝብ አስተያየት መመዘኛ መጠይቅ መሠረት፤ ጠ/ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ዳግም መመረጣቸው አይቀርም የሚል ጠንከር ያለ ግምት አለ። የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲና የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር

https://p.dw.com/p/17OsR
ምስል Reuters

አቪግዶር ሊበርማን ባይተኑ ፓርቲዎች ጥምረት፤ ከ 120 የፓርላማ መናብርት ሲሦውን ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ ይታሰባል። ሚንስትር አቪግዶር ሊበርማን ባይተኑ ፓርቲዎች ጥምረት፤ ከ 120 የፓርላማ መናብርት ሲሦውን ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ ይታሰባል።

ጠ/ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከሞላ ጎደል ጠንከር ያለ ፉክክር ሊያጋጥማችቸው የሚችለው፤ ከቀኝ አክራሪዎች በኩል እንደሚሆንይገመታል። «የአይሁድ ቤት » የተሰኘው በናፍታሊ ቤኔት የሚመራው ይበልጥ የቀኝ አክራሪ መሆኑ የሚነገርለት ፓርቲ 3ኛው ጠንካራ ፓርቲ ሆኖ ብቅ ማለቱ እንደማይቀርም ይነገራል።

ኔታናያሁ፣ በናፍታሊ ቤኔት ተባባሪነት ይበልጥ ወደቀኝ አክራሪነት ይገፋሉ? ወይስ በቆየው ተጣማሪ ፓርቲያቸው ያን እንዳያደርጉ ይገታሉ? አሳሳቢ የተባለው ጥያቄ ይህ ነው። ለምን ቢሉ? ከፍልስጤማውያን ጋር ለሚደረገው የሰላም ውይይት ሂደት ወሳኝነት አለው ተብሎ ይታመናልኛ! የጀርመንን ፌደራል መንግሥትም የሚያሳስበው ነጥብ ይኸኛው ነው።

Wahlen in Israel
ምስል Getty Images

የጀርመን የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት አባልና በቡንደስታኽ (የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት) የውጭ ጉዳዮች ተመልካች ኮሚቴ ሊቀመንበር Ruprecht Polenz ----

በአጭሩ ከዚህ ምርጫ በኋላ ከአሥራኤል ፓርላማ(ክኔሴት) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ጋር በተቀራረበ መልኩ ፣ ከሁለቱ ኮሚቴዎች ጋር ትብብር እንዲደረግ ስምምነት ላይ ለመድረስ እንጥራለን።»

ጀርመን ለእሥራኤል ደኅንነት ልዩ ታሪካዊ ኃላፊነት እንደሚሰማት የታወቀ ነው። ማንኛውም የጀርመን አስተዳደር ይህ መመሪያው ነው። እ ጎ አ ከ 2008 ዓ ም አንስቶ፤ የሁለቱ አገሮች መንግሥታት በያመቱ እየተገናኙ ይመክራሉ፤ የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን፤ የፓርላማዎቹ የውጭ ኮሚቴዎች ፖሌንትዝ እንደሚሉት ተባብሮ ለመሥራት የተስማሙ መሆናቸው እሙን ነው።

Wahlen in Israel Golan Höhen
ምስል MENAHEM KAHANA/AFP/Getty Images

የእሥራኤል የሠፈራ መርኅ ግብር ፤ በጀርመን ቅሬታን ከፈጠረ ቆይቷል። ይሁንና የጀርመን መንግሥት ግፊት በማድረግ መፍትኄ ማስገኘት እንደማይችል በዚሁ በጀርመን ለረጅም ጊዜ የእሥራኤል አምባሳደር የነበሩት አቪ ፕሪሞር ገለጸዋል።

Wahlen in Israel
ምስል Reuters

«የጀርመን መንግሥት ጣልቃ መግባት የሚችል አይመስለኝም። መግባትም የለበትም። ነገር ግን ከምርጫው በኋላ አዲስ አስተዳደር ሲመሠረት፤ (የጥምር መንግሥት መሆኑ ነው)ቅድመ ግዴታዎችን ማስቀመጥ ይቻላል።

የኛን ድጋፍ የምትሹ ከሆነ በፖለቲካው መርኅ የተጣጣመ አቋም ሊኖረን ይገባል። ምክንያቱም የመካከለኛው ምሥራቅ ፖለቲካ ሂደት ጀርመንንም ፣ አውሮፓንም ይመለከታልና!»

Wahlen in Israel
ምስል Reuters

እሥራኤል፣ ከጀርመን ጋር የሚያስተሣሥሩ ብዙ ጉዳዮች እንዳሏት የታወቀ ነው። ይሁንና ፣ የጀርመን የአረንጓዴው ፓርቲ ፖለቲከኛ ጀርዚ ሞንታግ፣ እንደሚሉት፤ በእሥራኤሉ ምርጫ ፣ ውጤቱ የቀኝ አክራሪዎችን ፍላጎት የሚያሣካ ከሆነ፤ አውሮፓውያኑ የሚወስዱት እርምጃ እምብዛም የሚያወላዳ አይሆንም፣ ይበልጥ ወደቀኝ የሚያዘነብሉት አክራሪ ወግ አጥባቂ እሥራኤላውያኑም ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠንከር የሚሹት ከዩናይትድ እስቴትስ እንጂ ከአውሮፓውያን ጋር አይሆንም። ስለዚህም ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሚያቀርቡትን የመፍትኄ ሐሳብ ጠብቆ ማየቱ ሳይሻል አይቀርም ። ጀርሲ ሞንታግ ፣ ለማንኛውም ለመካከለኛው ምሥራቅ ይበጃል ስላሉትና ከእሥራኤልም ስለሚጠብቁት እርምጃ እንዲህ ብለዋል።

«ተስፋ የማደርገው ከምር፤ ሳይድበሰበስ፣ ሁለት መንግሥታት ጎን ለጎን ለሚኖሩበት መፍትኄ የሚቆም መንግሥት እንዲመሠረት ነው። አዲሱ መንግሥት፤ በመለስተኛ የጊዜ ሰሌዳ፣ ከፍልስጤማውያን ጋር እርቅ የሚጀመርበትን መንገድ የሚሻም እንዲሆን ይጠበቅበታል።»

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ