የእሁዱ የፈረንሳይ የመታሰቢያ ሰልፍ
ሰኞ፣ ጥር 4 2007ማስታወቂያ
ሰልፉም በፈረንሳይ ታሪክ በርካቶች አደባባይ የወጡበት ሰልፍ እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ። ህዝባዊ ሰልፉ ፤ ሽብርተኝነትን በማውገዝ፣ አንድነትን እና ነፃነትን በሰበከ ሁኔታ ፤ በሰላም ተካሂዶ ተጠናቋል። የዘር፣ የሐይማኖት ፣ የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድባቸው፤ በአንድነት ሲቆሙ፤ በፈረንሳይ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎችም ሰንደቅ አላማቸውን ይዘው በመውጣት አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ይሁንና የባለፈውን ሳምንት ጥቃት ፈፃሚዎች፤ የአፍሪቃ ዝርያ ያላቸው ፈረንሳውያን መሆናቸው ከተነገር አንስቶ ፈረንሳይ ውስጥ የሚኖሩ በርካታ የሰሜን አፍሪቃ ፤ የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ደህንነታቸው ስጋት ላይ እንደወደቀ ይናገራሉ። የፓሪሷ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።
ሐይማኖት ጥሩነህ
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ