1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤ ኤን ሲ መሪ ጄኮብ ዙማ ችሎት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 29 2000

ቀጣዩ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው የሚባሉት የደቡብ አፍሪቃ የገዢው የአፍሪቃውያን ብሄረተኞች ኮንግረስ - የኤ ኤን ሲ መሪ ጄኮብ ዙማ በሙስናና በማጭበርበር ወንጀል የተመሰረተባቸውን ክስ ለማሰረዝ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

https://p.dw.com/p/EqyI
ጄኮብ ዙማ ከፍርድ ቤት ሲወጡ
ጄኮብ ዙማ ከፍርድ ቤት ሲወጡምስል AP

ብሄራዊው ዓቃቤ ህግ በዙማ ላይ በፒተርማሪትስቡርግ ላዕላይ ፍርድ ቤት የመሰረተው ክስ በፖለቲካ ምክንያት የተነሳሳ ነው በሚል የዙማ ጠበቆች ላቀረቡት ማመልከቻ ጉዳዩን ያዳመጡት ዳኛ ክሪስ ኒክልሰን መልሱን የፊታችን መስከረም ሁለት እንደሚሰቱ በማስታወቅ ችሎቱን ዘግተዋል።