1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ክስ፣ የኢትዮጵያ ምላሽና የፖለቲካ ተንታኝ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 26 2002

ኤርትራ የኢትዮጵያ ጦር ውጊያ ከፈተብኝ ስትል ያቀረበችውን ክስ ኢትዮጵያ ሀሰት ስትል አስተባብላለች ።

https://p.dw.com/p/LKuO
ምስል AP Graphics/DW

በኢትዮጵያ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ለዴይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት የኤርትራ ተቃዋሚዎች በኤርትራ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን እያስታወቁ ኤርትራ ኢትዮጵያን በጥቃቱ መወንጀሏ የውስጥ ችግር እንዳለባት ይጠቁማል ሲሉ አስታውቀዋል ። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ በበኩላቸዉ ኤርትራ ገደልኩና ማረኩ ስለምትላቸዉ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲሁም ተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የተከሰተዉ ሁኔታ በማስመልከት የአገራቱን ይዞታ በቅርቡ የሚያዉቁትን የኖርዌይ ዓለም ዓቀፍ ህግና ፖሊሲ ቡድን ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ኼቲል ትሩንቨል ተጠይቀዋል።

ዘገባዎቹን በቅደም ተከተል ማዳመጥ ይችላሉ።

ታደሰ እንግዳዉ/ ሂሩት መለሠ/ ሸዋዬ ለገሠ