1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ተቃዋሚዎችን የኤርትራ ፖለቲካ

ሰኞ፣ ነሐሴ 3 2002

የኤርትራ ተቃዋሚዎች ጥምረት አየፈጠሩ ነው። የኤርትራ ድሞክራሲያዊ ጥምረት 11 ፓርቲዎች የሚገኙበት ሲሆን በአዲስ አበባ የ10ቀናት ጉባዔ አካሂዷል።

https://p.dw.com/p/Og08
የኤርትራ ተቃዋሚዎችና ኢትዮጵያ
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ከስልጣን ለማውረድ ተቃዋሚዎች ትብብር ጀመሩምስል picture-alliance /dpa

ጥምረቱ ከጅምሩ መሰናክሎችን አላጣም። ከአባል ፓርቲዎቹ መሃል ያልተካፈሉም እንዳሉ ይነገራል። የኤርትራ ተቃዋሚዎች ስለህብረት አየተነጋገሩ ባሉበት በዚህን ወቅት የኢትዮዽያ ድጋፍ የኤርትራን ተቃዋሚዎች ምንያህል ውጤታማ ያደርጋቸዋል የሚለው እያነጋገረ ነው። ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ ተቃዋሚዎቹ ዓላማቸው ግልጽ አይደለም ይላሉ። የኤርትራ ዲሞክራሲያዊ ጥምረት ተወካይ ኤርትራ እስር ቤት ሆናለች በማለት የፕሮፌሰሩን ሃሳብ ያጣጥላሉ። የኤርትራ ተቃዋሚዎች በአዲስ አበባ ለ10ቀናት ያካሄዱትን ጉባዔ ሲያጠናቅቁ ለሚቀጥለው ዓመት ትልቅ ስብሰባ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል። በፓለቲካ ፓርቲዎቹ ማሃል ያለውን ልዩነትም ለማጥበብ ተስማምተዋል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ