የኤርትራ ስደተኞች UNHCR እና የኤርትራ መንግስት
ማክሰኞ፣ ኅዳር 15 2002ማስታወቂያ
በርካታ ኤርትራውያን ስደተኞች በየቀኑ ከሰላ ወደ ሚገኘው የስደተኞች መጠለያ እንደሚጎርፉ የሚናገረው UNHCR አብዛኛዎቹ ከጥቂት ጊዜያት በኃላ ከመጠለያ ሰፈሮቹ እንደሚጠፉ አስታውቋል ። ድርጅቱ እንደሚለው ኤርትራውያን ከሚሰደዱበት ምክንያት አንዱ ከብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ሽሽት ነው ። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ዜጎቼ ሀገራቸውን ጥለው የሚወጡት በውጭ ኃይሎች የተቀነባበረ ሴራ ነው ብሏል ። ጎይቶም ቢሆን
ጎይቶም ቢሆን ፣ ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ