የኤርትራ ሥደተኞችና እስራኤል
ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2005ማስታወቂያ
የእስራኤል መንግሥት በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሐገሩ የገቡ ሁለት ሺሕ ያሕል ኤርትራዉያን ስደተኞችን ወደ ሰወስተኛ ሐገር ለማጋዝ ማቀዱ ተዘግቧል።የእስራኤል መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት እስራኤል ሥደተኞቹን ለመቀበል ፍቃደኛ ለሆነች ለአዲት አፍሪቃዊት ሐገር የጦር መሳሪያና የዉጊያ ቴክኖሎጂ ለመስጠት ቃል ገብታለች።የተቀበይቱ ሐገር ማንነት በይፋ አልተነገረም።አንዳድ ምንጮች እንደሚሉት ግን ሥደተኞቹን ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነችዉ ሐገር አንድም ኢትዮጵያ አለያም ዩጋንዳ ናት።የሐይፋዉ ዘጋቢችን ግርማዉ አሻግሬ ጉዳዩን ተከታትሎታል።
ግርማዉ አሻግሬ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ