1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራዊዉ ስደተኛ መገደል

ሐሙስ፣ ጥር 7 2007

በጀርመን የኤርትራ ማሕበረሰብ አባላት ግፊት ካደረጉ በሕዋላ ግን ወጣቱ በሰዉ እጅ መገደሉን ፖሊስ አምኗል

https://p.dw.com/p/1ELGV
Lea-Sophie Tod Trauer Köln
ምስል picture alliance / dpa

ድሬዝደን-ጀርመን ዉስጥ ጥገኝነት ጠይቆ የነበረ አንድ ኤርትራዊ ወጣት በጩቤ ተወግቶ ተገደለ።የከተማይቱ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ኻሊድ በሚል የመጀመሪያ ሥሙ ብቻ የተጠቀሰዉ ወጣት የተገደለዉ ደረቱና አንገቱ በጩቤ ተጭቅጭቆ ነዉ።የድሬዝደን ፖሊስ መጀመሪያ በሰጠዉ መግለጫ የሃያ ዓመቱ ወጣት በሰዉ እጅ አልተገደለም ብሎ ነበር።በጀርመን የኤርትራ ማሕበረሰብ አባላት ግፊት ካደረጉ በሕዋላ ግን ወጣቱ በሰዉ እጅ መገደሉን ፖሊስ አምኗል። አቃቤ ህግ የግድያው ምክንያት እስካሁን ግልፅ አይደለም ሲል አስታወቋል ። እድሜው 20 ዓመት እንደሆነ የተገለፀውን ኤርትራዊ አስከሬን ማክሰኞ ጠዋት ከሚኖርበት ህንፃ በስተጀርባ ተጥሎ ማየታቸውን በአካባቢው ያልፉ የነበሩ ሰዎች አስታውቀዋል ። ኤርትራዊው ወጣት አንገቱ ና ደረቱ ላይ በተደጋጋሚ በስለት ተወግቶ መገደሉ ተነግሯል ። ግድያው በማንና በምን ምክንያት እንደተፈፀመ በመጣራት ላይ መሆኑን የድሬስደን ከተማ አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል ። ፖሊስ የአካባቢውን ነዋሪዎችና ከሟቹ ጋር አብረው የሚኖሩትን ስደተኞች በመጠየቅ ስለግድያው ፍንጭ ለማግኘት የሚያደርገውን ጥረት መቀጠሉም ተዘግቧል ። ሰኞ ማታ ሳይገደል እንዳልቀረ የተገመተው ኤርትራዊ ካለፈው መስከረም አንስቶ ድሬስደን ከተማ በሚገኝ ህንፃ ውስጥ ኤርትራውያን ከሚያመዝኑባቸው ሰባት ተገን ጠያቂዎች ጋር አብሮ ይኖር ነበር ። ድሬስደን ከጀርመን ከተሞች የውጭ ዜጎች ከሃገራችን ይውጡ የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች በብዛት ተጠናክረው የሚገኙባት ከተማ ናት ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሀመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ