የኤርትራዉያን ተቃዉሞ በዋሽንግተን ዲሲ
ዓርብ፣ የካቲት 1 2005ማስታወቂያ
ይኸዉ የተቃዉሞ ሰልፍ የተጠራዉ በቅርቡ አስመራ ዉስጥ የተደረገዉን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተቃዉሞ በመደገፍ መሆኑን ስምረት ኤርትራዉያን የተሰኘዉ የተቃዉሞ ሰልፉ አስተባባሪ ገልፀዋል። በዚሁ ሰልፍ ላይ የኤርትራ መንግስት ህገመንግስት እንዲፀድቅ፤ የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና ሰብዓዊ መብት እንዲከበር የሚሉና ሌሎች አስር ነጥብ የያዙ ጥያቄዎች ለኤርትራ ኤምባሲ እንደሚቀርቡ የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አመልክተዋል።
አበበ ፈለቀ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ