የኤርትራዉያን ስደት ዘጋቢ ፊልም
ዓርብ፣ መስከረም 30 2007ማስታወቂያ
ክስተቱ በወቅቱ የዓለም መገናኛ ብዙሃንን ከፍተኛ ትኩረት ለቀናት ይዞ ቆይቷል። ከሊቢያ የባህር ወደብ ወደአዉሮፓ ለመግባት በጀልባ ተጭነዉ የመጡ አብዛኞቹ ኤርትራዉያን የሆኑበት ጉዞ ካለሙት ሳይደርሱ ባህር ዉስጥ ማለቃቸዉ ብዙዎችን ከማሳዘን አልፎ መንስኤዉን እንዲያጤኑ ጋብዟል። ሁለት የጀርመን ARD ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችም ኤርትራ ሄደዉ ስደተኞቹ የተጓዙበትን 3,000 ኪሎ ሜትር በፊልም ቀርጸዉ እዉነታዉን በዘጋቢ ፊልም ለተመልካች አቅርበዋል። ፊልሙን የተመለከተዉ የበርሊን ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ጋዜጠኞቹን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ