1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራና የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ

ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2005

የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ ተደጋጋሚ ማስፈራራትና በደል ይፈፀምባቸዋል ያላቸዉ በካናዳ የኤርትራ ማሕበረሰብ አባላት የሚደርስባቸዉን ችግር መቋቋም እንደሚችሉ የኤርትራ መንግሥት እርግጠኛ ነዉ ቢልም ካናዳ የሚኖሩ ኤርትራውያን ግን በእርምጃው መደሰታቸውን አስታውቀዋል

https://p.dw.com/p/18hWC
ምስል AP Graphics


የካናዳ መንግሥት በቶሮንቶ የኤርትራ ቆንስላ ጄኔራልን ካገር እንዲወጡ ማዘዙን የኤርትራ መንግሥት አላስፈላጊ ትንኮሳ በማለት አውግዞታል። የካናዳ መንግሥት ኤርትራዊዉን ዲፕሎማት ያባረረዉ ካናዳ የሚኖሩ ኤርትራዉያን ከገቢያቸዉ ሁለት በመቶዉን ለአስመራ መንግሥት ግብር ያስከፍላሉ በሚል ነበር።የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መገለጫዉ እንዳለዉ ግን ዲፕሎማቱ ዓለም አቀፉንም ሆነ የካናዳን ሕግ የጣሰ ምግባር አልፈፀሙም።እርምጃዉንም «ኤርትራዉያን ከመንግሥታቸዉ ማግኘት የሚገባቸዉን አገልግሎት ለመንፈግ ያለመ፥ ትንሺቱን ግን ኩሩዋን ሐገር እና ሕዝቧን ለማስፈራራት የቃጣ» በማለት አዉግዞታል። የካናዳ መንግሥት የኤርትራን የቆንስላ ጽ/ቤት ከኤርትራውያን ላይ ግብር ከመሰብሰብ እንዲታቀብ ሲያስጠነቅቅ መቆየቱ ታውቋል። አዣንስ ፍራስ ፕረስ የጠቀሰዉ የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ ተደጋጋሚ ማስፈራራትና በደል ይፈፀምባቸዋል ያላቸዉ በካናዳ የኤርትራ ማሕበረሰብ አባላት የሚደርስባቸዉን ችግር መቋቋም እንደሚችሉ የኤርትራ መንግሥት እርግጠኛ ነዉ ቢልም ካናዳ የሚኖሩ ኤርትራውያን በእርምጃው መደሰታቸውን አስታውቀዋል
አበበ ፈለቀ--

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ