1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራና የኢትዮጵያዉያን የስደተኖች ፈተና

ሐሙስ፣ ጥቅምት 16 2004

የሱዳን መንግስት ጥገኝነት ፈልገዉ ከአገራቸዉ የተሰደዱ ኤርትራዉያንን ያለፍላጎታቸዉ ወደአገራቸዉ መለሱን የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አወገዘ።

https://p.dw.com/p/RtXD
ኮሚሽነር አንቶንዮ ጉተሬስምስል picture-alliance/ dpa

ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መቶች ተሟጋቹ ሂዉማን ራይትስ ዎች በበኩሉ ርምጃዉ ዓለም ዓቀፍ ህግን የጣሰ መሆን አመልክቷል። ሰሞኑን ብቻ የሱዳን መንግስት ወደአራት መቶ የሚደርሱ የኤርትራ ዜጎችን አስገድዶ ወደአገራቸዉ መመለሱን የድርጅቱ መግለጫ ያመለክታል። ተገደዉ ወደአገራቸዉ የሚመለሱት ኤርትራዉያን ብቻ እንዳልሆኑም እዚያዉ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ይናገራሉ።

ሶማሌላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በበኩላቸዉ UNHCR በደለን ይላሉ።ሀርጌሳ ሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ፣ የተበበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በእንግሊዘኛው ምህፃር UNHCR ተገቢ ድጋፍ አይሰጠንም ሲሉ አማረሩ ። ስደተኞቹ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ የሚሰጧቸው ልዩ ልዩ ድጋፎች ተቋርጠውባቸዋል ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ የሚገኘው የUNHCR ዋና መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አንድሬ ማሄቺች ግን ድርጅታቸው በስደተኝነት ለሚያውቃቸው ኢትዮጵያውያን ባለፈው ዓመት ባደረገው ማሻሻያ መሠረት እርዳታ እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል ። ሂሩት መለሰ ዝርዝሩን አዘጋጅታለች

ሸዋዬ ለገሠ

ሒሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ