1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣልያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈትና ስንብት

ረቡዕ፣ ሰኔ 18 2006

የኢጣልያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን፣ ፣ኮስታ ሪካ፤ ዑሩጓይና ኢንግላንድ ከሚገኙበት መ ምድብ፣ ትናንት ከዑሩጓይ ጋር ባደረገው ግጥሚያ እኩል ለኩል መለያየት ብቻ ለቀጣዩ ዙር ግጥሚያ ከኮስታሪካ ጋር በሁለተኛነት ለማለፍ የነበረው ዕድል በ 1-0

https://p.dw.com/p/1CQ0g
ምስል picture-alliance/dpa

ሽንፈት ከሽፎበት ከዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር ኢንግላድን አጅቦ ተሰናብቷል። የኢጣልያ ብሔራዊ ቡድን ከብራዚል ቀጥሎ በዛ ላለ ጊዜ (4 ጊዜ) የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ባለቤት ይሁን እንጂ፤ እ ጎ አ በ 1950,1954, 1962,1966,1974 እንዲሁም ከ 4 ዓመት በፊት በ 2010 በመጀመሪያ ዙር ላይ የተሰናበተ ቡድን ነው። ዘንድሮም ይኸው መጥፎ ዕጣ ገጥሞታል። በኢጣልያ ፣ እግር ኳስ አፍቃሪው ሕዝብ ምን ይሆን የተሰማው? የሮማውን ዘጋቢአችንን ተክለ እግዚአ ገብረ-የሱስን በስልክ ጠይቄው ነበር።

ተኽለዝጊ ገ/የሱስ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ