1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣልያ መንግሥት በስደተኞች ላይ የወሰደው ብርቱ እርምጃ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2001

የኢጣልያ መንግሥት፣በ 5 ቀናት ውስጥ፣ ከሜድትራንያን ባህር 557 ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሊቢያ መመለሱ ታውቋል።

https://p.dw.com/p/Hoi4
ምስል AP

እንዲመለሱ ከተገደዱት መካከል፣ 2 ነፍሰ-ጡሮችና ከተወለዱ 2 ቀን የሆናቸው ህጻናት እንደነበሩበት ለማወቅ ተችሏል። የኢጣልያ መንግሥት የሰብአዊነት መንፈስ በጎደለው እርምጃ ወደ ሊቢያ የመለሳቸው ስደተኞች፣ አብዛኞቹ የአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ ሀገራት ተወላጆች ሲሆኑ፣ ከሊቢያ መዲና ከትሪፖሊ 30 ኪሎሜትር ራቅ ብሎ በሚገኝ እሥር ቤት መታጎራቸውም ተመልክቷል። የሰደተኞቹ የወደፊት ዕጣ-ፈንታ ምን ይሆን ? ለሚለው ጥያቄ አሁን መልሱን ማግኘት አልተቻለም ። ሊቢያ ስደተኞቹን፣ አስገድዳ ወደየትውልድ አገሮቻቸው ከመለሰቻቸው፣ ህይወታቸው ብርቱ አደጋ ላይ ይወድቃል ተብሎ ነው የተሠጋው።

ተኽለዝጊ ገ/የሱስ/ተክሌ የኋላ/አርያም ተክሌ