የኢጣሊያ ጦር ዘመቻና የማርሻል ኢፍጣር ትዕዛዝ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2009ማስታወቂያ
ምሥራቃዊ ሊቢያን የሚቆጣጠረዉ ጦር አዛዥ ኸሊፋ ሐፍጣር ወደ ሊቢያ የባሕር ክልል ያለፍቃድ የሚገባ የዉጪ ጦርን እንደሚመቱ አስጠነቀቁ።ለራሳቸዉ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ያጠለቁት ሐፍጣር ዛሬ እንዳስታወቁት ጦራቸዉ በራስ ላኑፍ፤ጡብሩክ እና በትሪፖሊ በኩል የሚገባ የዉጪ ጦርን እንዲመታ ታዝዟል።የማርሻሉ ማስጠንቀቂያ የተሰማዉ፤ ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን ታድናለች የተባለች አንዲት የኢጣሊያ ቃኚ ጀልባ ባካባቢዉ ሊቢያ ጠረፍ ከደረሰች በኋላ ነዉ።የቀድሞዉ የሊቢያ ቅኝ ገዢ ኢጣሊያ ሊቢያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ስደተኛ አሸጋጋሪዎችን የሚያድን ጦር እንድታዘምት የሐገሪቱ ምክር ቤት ትናንት ወስኗል።ሥለዘመቻዉ ዉሳኔና ዓላማ የሮም ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረየሱስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ተኽለእዝጊ ገብረእየሱስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ