የኢአዲድ እና የመኢአድ መግለጫ8 ነሐሴ 2004ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2004የኢትዮጵያውያን አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ኢአዲድ እና የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት መኢአድ በደቡብ ግዛት ውስጥ በአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ የመፈናቀል እና የሠብዓዊ መብት ጥሰት ደርሷል ሲሉ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።https://p.dw.com/p/15pazማስታወቂያ ድርጅቶቹ የጋራ መግለጫቸውን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ኤምባሲዎች እና ለጋዜጠኞች የላኩ መሆናቸውን ከመግለፃቸውም ባሻገር ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል። የሠብዓዊ መብቶች ጉባኤም ችግሩን በተመለከተ አቤቱታ እንደደረሰው እና በቦታው ላይ ማጣራት እያደረገ እንደሆነ በተጠባባቂ ሊቀመንበሩ በኩል ገልጿል። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ማንተጋፍቶት ስለሺ ሸዋዬ ለገሰ