የኢንተርኔት ዓለም-አቀፍ የመረጃ ድር፣ 20ኛ ዓመት፤
ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2001ማስታወቂያ
እኒህ ሰው፣ እስዊትስዘርላንድና ፈረንሳይ ድንበር ላይ በሚገኘው የአቶም ምርምር ጣቢያ(CERN)ውስጥ ከሌሎች 3 ባልደረቦቻቸው ፣ Robert Cailliau, Ben Segal እና Jean-Francois Groff ጋር ሆነው እዚህ ደረጃ ያበቁት የኮምፒዩተር የመረጃ መረብን ሆነ ድር የተፈለሰፈው እ ጎ አ በመጋቢት ወር 1989 ዓ ም ሲሆን፣ ለህዝብ አግልግሎት መስጠት የጀመረው፣ እ ጎ አ ከ 1993 ዓ ም ወዲህ ነው።
በኦክስፎርድ ፊዚክስ ካጠኑ በኋላ፣ በ CERN ለመመራመር ወደ ጀኒቭ ያመሩት ቲም በርነርስ ሊ፣ ከ 20 ዓመት በፊት የ «ሶፍት ዌር ኢንጅኒየር » በነበሩበት ጊዜ፣ ለአለቃቸው ማይክል ሴንዶል፣ መረጃእንዴት ሊቀርብና ሊያዝም እንደሚችል ሐሳብ አቅርበው ፣ አለቃቸው እንደዋዛ ይቀበሉላቸዋል።
ዓለም አቀፍ የመረጃ ግንኙነትን እንዲሠምር ሊያደርግ የሚችለው፣ በጽሑፍ የቀረበው ሐሳብ፣ ውስብስብ ያለና ፣ ክብ የተደረገበት ስዕል ነበረበት። ማዕከሉ ላይም Mesh የሚል ስም የተጻፈበት ነበረ። ሆኖም በርነርስ-ሊ፣ “Mesh” ፣ “Mess“ (ዝብርቅርቅ) የሚል ዓይነት ድምፅ ስላለው፣ ስሙን መለወጥ ፈለጉና፣ እ ጎ አ በ 1990 ዓ ም፣ World Wide Web የተሰኘውን ስያሜ ሰጡት።
AFP/Wikipedia
ተክሌ የኋላ፣
ሸዋዬ ለገሠ፣