የኢንተርኔት አገልግሎት እገዳ በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 4 2010ማስታወቂያ
አንጡራ ወይም የእንግሊዝኛ ሥሙ ኢንተርኔት ነዉ።አንዳዶች አምደ-መረብ ይሉታል።ሌሎች በይነ-መረብ።ብዙዎች ያዉ እንደ ገና ስሙ ኢንተርኔት።ኢንተርኔትም አልነዉ ሌላ አገልግሎቱ ያዉ ነዉ።ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ ዉስጥ ይሕን አገልግሎት የሚጠቀመዉ ከሐገሪቱ ሕዝብ አስራ-አምስት ከመቶ ቢሆን ነዉ።ይሕ አልበቃ ብሎ፤ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ነፃነትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚደፈልቁ ሐገራት አንዷ መሆንዋን በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት አጋልጧል።የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ፕሮጄክት የተባለዉ ተቋም ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አገልግሎቱን ከማስፋፋት ይልቅ ለመገደብ እና ተጠቃሚዎችን ለመሰለል የሚያወጣዉ ገንዘብም ብዙ ነዉ።የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ