1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ጅቡቲ የውኃ አቅርቦት ስምምነትና ፋይዳው

እሑድ፣ ሰኔ 15 2006

ስምምነቱ በዋነኛነት የጅቡቲ ወደብ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆነችው ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን መንግሥት ይናገራል።በዚህ የሚስማሙ ወገኖች እንዳሉ ሁሉ የዜጎች የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር ሳይሟላ ለሌላ አገር ውኃ ለማቅረብ መስማማት ተገቢ አይደለም የሚሉም አልጠፉም ።

https://p.dw.com/p/1CNIQ
Nomadin hütet Ziegen in Äthiopiens Krisenregion Ogaden
ምስል picture alliance/dpa

ከፍተኛ የውኃ እጥረት ያለባት ጅቡቲ ከጎረቤት ኢትዮጵያ በነፃ ውኃ ማግኘት የሚያስችላት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ከተፈራረመች ዓመት ከመንፈቅ አልፏል ። በዚሁ ስምምነት ላይ ያተኮረ ረቂቅ አዋጅ በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል ። ስምምነቱ በዋነኛነት የጅቡቲ ወደብ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆነችው ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን መንግሥት ይናገራል። በዚህ የሚስማሙ ወገኖች እንዳሉ ሁሉ ዜጎች ያለባቸው የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር ሳይሟላ ለሌላ አገር ውኃ ለማቅረብ መስማማት ተገቢ አይደለም የሚሉም አልጠፉም ። የኢትዮ ጅቡቲ የውኃ አቅርቦት ስምምነትና ፋይዳው የእንወያይ ትኩረት ነው።

ሂሩት መለሰ

ልደት አበበ