የኢትዮ ኬንያ የኤልክትሪክ መሥመር ዝርጋታ፤29 ሐምሌ 2008ዓርብ፣ ሐምሌ 29 2008የኢትዮጵያ እና ኬንያ የጋራ የኤሌክትሪክ መሥመር ዝርጋታ ሥራ በይፋ ተመርቆ መጀመሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ። አንድ ሺህ 45 ኪሌ ሜትር እንደሚሸፍን የተገለጸዉ የኤሌክትሪክ መሥመር 2 ሺህ ሜጋ ዋት ኃይል የመሸከም አቅም እንዳለዉ ተገልጿል።https://p.dw.com/p/1JcMLምስል DWማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ከዚህ ዉስጥም 600 ኪሎ ሜትሩ በኬንያ ግዛት ቀሪዉ 445 ደግሞ በኢትዮጵያ ግዛት ዉስጥ የሚዘረጋ ነዉ። ፕሮጀክቱም እስከ መጪዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2018 ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ናይሮቢ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ። ፋሲል ግርማ ሸዋዬ ለገሠ ነጋሽ መሐመድ