1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጽያ እና የኖርዊይ ግንኙነት መሻሻል

ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2001

ኢትዮጽያ እና ኖርዊይ የወዳጅነት ግንኙነታቸዉን እንደሚያስተካከሉ ገለጹ። ባለፈዉ ረቡዕ የኖርዊዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዮናስ ጋር ስቶር እና የኢትዮጽያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ስዪም መስፍን በኒዉዮርክ በተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ላይ ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸዉን እንደገና ማደሰስ እንደሚሹ ስምምነታቸዉን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/FUxj

ኢትዮጽያ ባለፈዉ አመት መስከረም ወር ላይ የኖርዊይ በምስራቅ አፍሪቃ ያለዉን ጸጥታ እየነሳች ነዉ ስትል ስድስት የኖርዊይ ዲፕሎማቶችን ማባረርዋ የሚታወስ ነዉ። በኢትዮጽያ እና በኖርዊ መካከል ስለተፈጠረዉ ቅሪታ እና እርቅን በተመለከተ ኖርዊይ በኢትዮ ኤርትራ መካከል ያለዉን የድንበር ዉዝግብ ለመፍታት አለኝ የምትለዉ ሚና አስታራቂ ሃሳብ በኢትዮጽያ መንግስት ላይ ቅሪታን አሳድሮ ነበር በኢትዮጽያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በተለይ ለዶቸ ቬለ ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል